የሊዝ ጨረታ ማስታወቅያ
02/10/2017
#የመሬት_ሊዝ_ጨረታ_ማስታወቂያ!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀላባ ዞን የቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት በ12 ኛው ዙር በከተማው ውስጥ የሚገኙ ለመኖሪያና ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በመደበኛ የሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከሀላባ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ከመሬት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በስራ ሰዓት በግንባር ቀርበው የማይመለስ ብር 900 (ዘጠኝ መቶ) ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
👉 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0465560008 / 0912122401 /
ደውለው መጠየቅ ይችላሉ!
👉 በተጨማሪም በዌብሳይት አድራሻችን www.halabamun.gov.et ይጎብኙን።
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት